Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ፑቲንና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በኒው ደልሂ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ህዳር 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኒው ደልሂ ተገናኝተው ተወያዩ።

መሪዎቹ በበርካታ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፥ ያንን ተከትሎም ሀገራቱ 28 ስምምነቶች ተፈራርመዋል።

መሪዎቹ በውይይታቸዉ ከሽብርተኝነት እና ከአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ቅድመ መከላከል ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድረገዉ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተላቸው ተግዳሮቶች ቢኖሩም በህንድ እና በሩሲያ መካከል ያለው ግንኙነት ላይ ግን ያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ በወረርሽኙ ወቅት ሁለቱ ሀገራት በክትባት እና በሰብአዊ ድጋፍ ዙሪያም በትብብር ሲሰሩ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢኮኖሚው ዘርፍ ያለው ትብብር ጥሩ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁመው፥ በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ሀይላቸዉን ለማጠናከር በስትራቴጂካዊ አጋርነት እንደሚሰሩ አመላክተዋል፡፡

ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸዉ ኢነርጂ እና የጠፈር ምርምርን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች ላይ ሁለቱ ሃገራት በትብበር እየሰሩ መሆናቸዉን ገልፀዋል፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ሁለቱ ሀገራት በዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተባብረው እንደሚሰሩ በመግለፅ፥ ሽብርተኝነት እና የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን መከላከል የሚቻልባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ተናገረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በየሀገሮቻቸው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸውን ጠቁመው፥ ሩሲያ በቀጣይም በወታደራዊ ልምምድ ዙሪያ ከህንድ ጋር የበለጠ ለመስራት መዘጋጀቷን ነው ያረጋገጡት።

በሚኪያስ አየለ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.