Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾመዋል።

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በፓለቲካ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ከቆዩ አንጋፋ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው።
 
በአሁን ወቅት የተፎካካሪ ፓርቲው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
 
ፕሮፌሰር በየነ የተለያዩ ፓርቲዎችን በአባልነት የያዘውን የመድረክ ፓርቲንም በሊቀመንበርነት መርተዋል።
እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በመምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩ ምሁር ናቸው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.