Fana: At a Speed of Life!

ፖለቲከኞች አገር መውደድን፤ ለስልጣን ሳይሆን ለአገር መሞትን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሊማሩ ይገባል – እውቁ ቱኒዚያዊ ጋዜጠኛ ሳልህ አል-አዝረቅ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሸባሪውን ቡድን ለመዋጋት ወደ ግንባር መዝመታቸው አገር ከስልጣን በላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ሲል እውቁ ቱኒዚያዊ ጋዜጠኛ ሳልህ አል-አዝረቅ።
 
ጋዜጠኛው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር መዝመት አገራችውን ምን ያክል እንደሚወዱ የሚያሳይ እና አገር ከስልጣን በላይ፤ ስስልጣን ከአገር በታች መሆኑን ለመላው የዓለም ህዝብ ያስተዋወቀ ነው ብሏል።
 
በዘገባው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ግንባር መዝመት በሌሎች አገራት ያልተለመደ ቢሆንም በኢትዮጵያውያን ዘንድ ግን የተለመደ የጀግንነት ታሪክ መሆኑን አንስቷል።
 
አያይዞም የትኛው የአረብ ፓርላማ አባል ወይም የመንግስት ባለስልጣን ስልጣኑን ጥሎ ለአገሩ ሊዋጋ ጫካ የወረደው? ሲልም ይጠይቃል።
 
ከዚህ ጋር ተያይዞም በአንዳንድ አገራት መሪዎች ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ የሄዱበትን መንገድ በማንሳት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባር መዝመት በአድናቆት ተመልክቶታል።
 
የምዕራባውያን ተላላኪ ስርአት አገሬ ላይ ከሚሰፍን እዋጋለሁ በማለት ለማንም የማይላላኩ መሪ መሆናቸውን አሳይተዋልም ነው ያለው ጋዜጠኛው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.