Fana: At a Speed of Life!

ፖሊስ የሰሜን ዕዝ ሎጂስቲክ ምክትል ኃላፊ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ከድር የጦር መሳሪያ ማከማቻ የት እንደሚገኝ ለህወሓት የጸረ ሰላም ቡድን መረጃ ሲያቀብሉ ነበር አለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ዕዝ ሎጂስቲክ ምክትል ኃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ከድር አራርሶ የጦር መሳሪያ ማከማቻ እና ተተኳሽ የጦር መሳሪያዎች የት እንዳሉ ለህወሓት የጸረ ሰላም ቡድን መረጃ ሲያቀብሉ እንደነበር ፖሊስ ገለጸ፡፡

በዚህ መረጃ መሰረት የጦር መሳሪያው እንዲዘረፍና ወደ ትግራይ ልዩ ኃይል እንዲተላለፍ በሰጡት ጥቆማ መሰረት መደረጉን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው ኃላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው በትግራይ ክልል የነበሩ የጦር መሳሪያዎች ከዚያ እንዳይወጡ ሲያደርጉ እንደነበር ያገኘሁት ማስረጃ ያመላክታል ብሏል፡፡

ተጠርጣሪው ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡

ፖሊስም በርካታ ምርመራ መስራቱን ገልጾ ተጨማሪ ምርመራ ለማከናወን 14 ቀን ጠይቋል፡፡

ተጠርጣሪው ተተኳሽ የጦር መሳሪያዎች ከትግራይ ክልል እዳይወጡ ከዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ጋር ምክክር ተደርጎ መሳሪያው እዚያው እንዲቆይ መደረጉን ጠቁመው ወንጀሉ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው በመግለጽ በነጻ ወይም በዋስ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

የግራ ቀኙን የተመለከተው ችሎትም ለመርማሪ ፖሊስ 11 ቀናትን ፈቅዶለታል፡፡

በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.