Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 496ኛው የመውሊድ በዓል የፊታችን ሰኞ ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 496ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) የፊታችን ሰኞ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።
በዓሉን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ÷ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ነቢዩ መሐመድ የተወለዱት መልካም ነገሮችን ሊያስተምሩና መጥፎ ነገሮችን ደግሞ ሊቃወሙ በመሆኑ መልካም ስራቸውን በማየት በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ መውሊድ ይከበራል ብለዋል።
በዓሉ ሲከበር የነቢዩ መሐመድን በረከቶች በማስተዋልና መንገዳቸውን በማሰብ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አቅም የሌላቸውን በመጎብኘትና ካለው በማካፈል እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል።
ተቀዳሚ ሙፍቲው በአገሪቷ ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ገንዘብ በማሰባሰብ በሠላም ሚኒስቴር በኩል በተዘጋጀ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ መደረጉንም ገልጸዋል።
መንግስት በተለያየ ችግር ላይ ያሉ ዜጎችን መደገፍና ድጋፉም ለተጎዱ መድረሱን ሊያረጋግጥ እንደሚገባም ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ አመልክተዋል።
የመውሊድ በዓል የሠላም እንዲሆን መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል።
አገራችንን አላህ አማን ያድርግልን፣ የአውሬ ጸባይ ከሰው ጸባይ ላይ አላህ ያንሳልን፣ የሚያፈቃቅር የሚያቀራርብ የሚያመካክር ነገር አላህ ይስጠን ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.