Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 76 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 76 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ።

1 ሺህ 76 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን÷ ከተመላሾቹ ውስጥም 705 ወንዶች፣ 154 ሴቶች እና 217ቱ ሕጻናት መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉ ተገልጿል፡፡

እስካሁን በተከናወነው ስራ ቁጥራቸው ከ 27 ሺህ 956 በላይ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ ዓረቢያ መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.