Fana: At a Speed of Life!

1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በመዝረፍ ወንጀል የፈጸሙ ተከሳሾች በ16 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በመዝረፍ ከባድ የውንብድና ወንጀል የፈፀሙ ሁለት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው።

1ኛ ተከሳሽ አስር አለቃ ሃብታሙ ገ/ኪሮስ እና 2ኛ ተከሳሽ ዘካርያስ ባጫ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ እና 671 /1/ለ ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ተላልፈው ተገኝተዋል ተብሏል።

በዚህም ሚያዝያ 22 ቀን 2012 ዓ.ም  በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ”ቤቴል እሳት አደጋው”  ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የግል ተበዳይ የያዘውን መኪና 1ኛ ተከሳሽ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር  መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ የኮሌጅ ሾፌር በመሆን ለስራ የሚገለገልበትን መኪና በመጠቀምና የተበዳይን መንገድ በመኪናው ሲዘጋበት 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ ተበዳይን በመኪናው መስኮት በመግባትና ገፍትሮ በማስወረድ 1ኛ ተከሳሽ ወደያዘው መኪና አስገድዶ በማስገባትና በማሰር ከመኪና ኮፈን ውስጥ በቦርሳና በፌስታል  የነበረ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በመዝረፍ እና ለዐቃቤ ህግ ምስክር አሳልፈው በመስጠት ወንጀል መፈጸማቸውን በዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ተመልክቷል፡፡

በዚህም መሰረት ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነትና ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት ከባድ የውንብድና ወንጀል በሁለት የተለያዩ ክሶች በዐቃቤ ህግ ክስ  ተመስርቶባቸዋል።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም ዐቃቤ ህግ በዝርዝር ያቀረበው ማስረጃ የተከሳሾችን ጥፋተኝነት በትክክል ያስረዳ በመሆኑ ተከሳሾችን ጥፋተኛ ናችሁ ሲል እያንዳንዳቸው በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.