Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 20 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 20 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ዜጎች መካከል ሦስቱ ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸውንየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ ተደርጎላቸው ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት መሄዳቸው ተመላክቷል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ÷ 63 ሺህ 467 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.