Fana: At a Speed of Life!

10ኛው የጨርቃ ጨርቅና ፋሽን ዓለም አቀፍ ጉባኤ በባህር ዳር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) 10ኛው የጨርቃ ጨርቅና ፋሽን ዓለም አቀፍ ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

ጉባዔው በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ እና የኢትዮጵያ ቴክስታይል ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን፥ በዘርፉ የሚንቀሳቀሱ የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችም ተሳትፈውበታል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶክተር ታምራት ተስፋዬ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ፥ የጉባዔው ዋና አላማ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍትሄ ማበጀትና ኢንዱስትሪዎች የሚጠናከሩበትን አቅጣጫዎች ማመላከት ነው።

እንደ ዳይሬክተሩ ከዚህ ቀደም የጥጥ ምርቶችን በተመለከተ መንግስታዊ ተቋም የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመው ፥ በዘርፉ የሚንቀሳቀሱ ባለሙያዎችም ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት እድሎች ሲመቻቹ ቆይተዋል ብለዋል።

በጉባዔው ልዩ ልዩ ጥናታዊ ፅሁፎችና የልምድ ተሞክሮዎች የቀረቡ ሲሆን፥ ዘመኑን የዋጁ የጨርቃ ጨርቅና ቆዳ ውጤቶችም ለእይታ ቀርበዋል።

በሙሉጌታ ደሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.