Fana: At a Speed of Life!

10 ክላሽ እንኮቭና ከ5 ሺህ በላይ ህገ ወጥ የቱርክ ሽጉጥ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር 10 ክላሽ እንኮቭ እና 5 ሺህ 681 ህገ ወጥ  የቱርክ ሽጉጥ ጥይት  መያዙን ተገለፀ፡፡

የጦር መሣሪው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በሳንጃ ጉምሩክ ቅርንጫፍ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጉምሩክ ፈታሽ ባለሙያዎችና በአማራ ልዩ ኃይል በተደረገ ፍተሸ መያዙ ነው የተነገረው፡፡

ህገ ወጥ የጦር መሳርያው መነሻውን ከጠገዴ ወረዳ ሶሮቃ ከተማ  ጎንደር ባደረገ ደብል ፒካብ ተሽከርካሪ በ3ቱ በር በኩል 5 ሺህ 681 የቱርክ ሽጉጥ ጥይትና 10 ክላሽ ኮፍ  ወደ ጎንደር ለማለፍ ሲሞክር እንደተያዘ  ከየታች አርማጭሆ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አሽከርካሪውም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርምራ እየተደረገበት እንደሆነ ተጠቁሟል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.