Fana: At a Speed of Life!

12ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል ዛሬ ፍፃሜውን አገኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረዉ 12ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት ሲካሄድ የሰነበተው የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አጠቃላይ አሸናፋነት ነው የተጠናቀቀው ፡፡
በባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሀም ታደሰ፥ ፌስቲቫሉ የዕርስ በዕርስ ግንኙነትን ከማጠናከር አንፃር ትልቅ ሚና እንደነበረውና ለሀገር አቀፍ ውድድሮች የሚመጥኑ ስፖርተኞች ተገኙበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የቢሮው ሃላፊ አክለውም ይህ ውድድርና ፌስቲቫል እንዲሳካ የላቀ አስተዋፅኦ ላደረገው የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በከተማ አስተዳደሩና በራሳቸው ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.