Fana: At a Speed of Life!

12 ቋንቋዎችን አቀላጥፎ የሚናገረው የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩኒቭርስቲ ቆይታው ተጨማሪ 6 ቋንቋዎችን አቀላጥፎ በመናገሩ በዩንቨርስቲው እንዲቀጠር እና 2ተኛ ዲግሪ እንዲማር እድል ተሰጥቶታል፡፡

አደም ከድር በሶሾሎጂ የተመረቀ ሲሆን አፋን ኦሮሞ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ አረብኛ፣ ሱዳንኛ፣ ሰልጤኛ፣ ሀዲየኛ ና ሌሎችንም አቀላጥፎ ይናገራል ።

የአፍ መፍቻ ቋንቋው ሲዳምኛ ሲሆን ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጣ 6 ቋንቋዎችን ይናገር ነበር።
አደም በዩኒቭርስቲ ቆይታው ይህንን የቋንቋ ችሎታውን ወደ 12 ማሳደግ ችሏል።

ዩኒቨርስቲውም አደም በነበረበት የማህበረሰብ ሳይንስና ሂዩማኒቲ ኮሌጅ ላደረገው የነቃ ተሳትፎ እና ለልዩ ችሎታው በዩንቨርስቲው እንዲቀጠር እና 2ተኛ ዲግሪ ትምህርቱን እንዲማር እድል ሰጥቶታል።

በቅድስት ዘዉዱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.