Fana: At a Speed of Life!

125ኛው የአድዋ ድል በዓል በኬንያ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛው የአድዋ ድል በዓል ዛሬ የካቲት 20 ቀን 20213 ዓ.ም በኬንያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት በበይነ-መረብ ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ በኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነት አገልግሎት አካዳሚ ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ማይክ ኦዩንግ፣ ተጋባዥ አምባሰደሮች እና በኬንያ የሚኖሩ የዲያፖራ አባላት ተሳትፈዋል።

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው አድዋ በጥቁር ህዝቦች የተመዘገበ አንፀባራቂ ድል ነው ብለዋል።

የነጮች የበላይነት አስተሳሰብ መሠረት የተናደበት ነበርም ብለዋል።

ይህ ደግሞ ለአፍሪካ ነጻነት እና ለፓን አፍሪካኒም ፍልስፍና መነቃቃት ብሎም ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመሰረት አይነተኛ ሚና እንደነበረው አሰረድተዋል።

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም የአድዋ ድል ሁሉም ኢትጵያውያን በአንድነት ተነስተው የጣሊያን ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ምኞት ያከሸፉበት እንደነበር ተናግረዋል።

በኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነት አገልግሎት አካዳሚ ዳይሬክተር ጄኔራል የሆኑት አምባሳደር ማይክ ኦዩንግ የአድዋ ድል ታሪካዊ እና የመላው አፍሪካ ብሎም የሁሉም ጥቁር ህዝቦች የኩራት ምንጭ መሆኑን ተናግረዋል።

ድሉ የኢትዮጵያን ነጻነት ከማረጋገጡም በተጨማሪ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና በጃፓን ጭምር ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥሮ እንደነበር አምባሳደሩ አሰረድተዋል።

በተጨማሪም የኬንያ ነጻነት አባት በመባል ለሚታወቁት ለቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ጆሞ ኬንያታ የአድዋ ድል የሞራል ስንቅ እንደነበር አምባሳደር አዩንግ ተናግረዋል።

የአድዋ ድል ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.