Fana: At a Speed of Life!

125ኛው የዓድዋ የድል በዓል በመላ ኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛው የዓድዋ የድል በዓል በመላ ኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በአዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላትን እና በርካታ እንግዶች ታድመዋል።

በተመሳሳይ በመስቀል አደባባይም በርካታ የፌዴራል፣ የክልል እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ፈረሰኞች እና ታዳሚዎች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

በመላ ሀገሪቷም በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.