Fana: At a Speed of Life!

125ኛውን የአድዋ ድል በማሰብ የተጀመረው ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛውን የአድዋ ድል በማሰብ የተጀመረው 12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በባህርዳር ስታዲየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ቡናና የወልቂጤ ከተማ ጨዋታ በማርሽ ባንድ ታጅቦ የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙር በመዘመር ነበር የተጀመረው፡፡

በጨዋታውም ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ለኢትዮጵያ ቡና ግቦቹን አቡበከር ናስር በ4ኛው ደቂቃና በ58ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

ለወልቂጤ ከተማ ደግሞ አቡበከር ሳኒ በ73ኛው ደቂቃ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡

ፕሪምየር ሊጉን ፋሲል ከነማ 13 ጨዋታዎችን አድርጎ በ32 ነጥቦች ይመራል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና በ13 ጨዋታዎች 27 ነጥቦችን በመያዝ ሲከትል ቅዱስ ጊዮርጊስ በ24 ነጥቦች ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ከሰዓት በሚካሄደው መርሃ ግብር ሲዳማ ቡናና ባህርዳር ከተማ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.