Fana: At a Speed of Life!

125ኛውን የአድዋ ድል በዓል በሁሉም ክልሎች እንዲከበር ሲሰራ የቆየው ስራ ስኬታማ እንደነበር ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ125ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አከባበር በማስመልከት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል አከባበር ለየት የሚያደርገው ሕብረተሰቡ ስለ አድዋ ድል የራሱ ታሪክ አድርጎ እንዲይዘው ግንዛቤ የተፈጠረበት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
እንዲሁም በዓሉ እስከ ወረዳ ድረስ ወርዶ እንዲከበር መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሯ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚኖሩ የማጠቃለያ መርሐ ግብሮችን ዝርዝር የገለፁ ሲሆን በመርሃ ግብሩም ከየካቲት 19 እስከ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም የስዕልና ቅርጻ ቅርጽ አውደ ርዕይ፣ የፎቶና መጽሃፍት አውደ ርዕይ፣ የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ሚኒስትሯ በዓሉን የሚገልጽ ቴአትር፣ የአድዋ ታሪክ በምሁራን እይታ የሚል የፓናል ውይይት፣ በብሔራዊ ሙዚየም፣ በብሔራዊ ቴአትር፣ በኩባ ወዳጅነት ፓርክ፣ በአንድነትና በወዳጅነት ፓርክ ይካሄዳል ማለታቸውን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.