Fana: At a Speed of Life!

13ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 300 ሺህ ሰዎች እንደሚሳተፉበት የሚጠበቀው 13ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ፌስቲቫል በግዮን ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።
የባህል ፌስቲቫሉ “የባህል እሴታችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መልዕክት ነው እየተካሄደ ያለው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል፣ቱሪዝምና ኪነ ጥበብ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳውን ጨምሮ የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በፌስቲቫሉ ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው ፥የፌስቲቫሉ ዋነኛ ዓላማ የማህበረሰቡን ወግ፣ ባህልና በጎ የሆኑ ማህበራዊ እሴቶችን ማስተዋወቅ ነው ብለዋል።
የብሔር ብሔረሰቦች የባህል፣ የእደ ጥበብ ውጤቶች፣ ባህላዊ የግጭት አፈታትና ሌሎች ክዋኔዎች ለህዝብ የሚተዋወቁ መሆኑን ጠቅሰው፥ ፌስቲቫሉ አምራቾችና ሻጮች የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩም የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ባህላዊ ምግብና መጠጦች፣ አልባሳት የዲዛይን ውድድሮችና ሌሎች ሁነቶች ይከናወንበታል ነው ያሉት።
አገር በቀል እውቀቶች እንዳይጠፉ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ተደግፈው ለትውልድ ማስተዋወቅና ማስተላለፍ ስለሚቻልባቸው አማራጮች ላይ የምሁራን ውይይት የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል።
ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚሁ ፌስቲቫል፥ የተለያዩ የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህል፣ አኗኗር እና አለባበስ የሚያሳዩ ትዕይንቶች እንደሚቀርቡ ሪፖርተሮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.