Fana: At a Speed of Life!

130 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ሰሊጥ ወቅቱን ባለጠበቀ ዝናብ እንዳይጎዳ እየተሰበሰበ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ለውጭ ገበያ የሚቀርብ በ130 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ሰሊጥ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይጎዳ በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኝ የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

እየተሰበሰበ ያለው የሰሊጥ ምርት ከህልውና ዘመቻው ጎን ለጎን በ2013/14 ምርት ዘመን በባለሃብቶችና አርሶ አደሮች የለማው ነው።

በዞኑ በስፋት የሚመረተውና የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኘው ሰብል ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ጉዳት እንዳይደርስበት በፍጥነት እየተሰበሰበ መሆኑን በመምሪያው የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ሞገስ ጋሹ ተናግረዋል።

በሰሊጥ ሰብል ከለማው መሬት ውስጥ 50 ሺህ ሄክታር በእርሻ ኢንቨስትመንት በተሰማሩ ባለሃብቶች የለማ፤ ቀሪው ደግሞ በአርሶ አደሮች መልማቱን ገልጸዋል።

ባለሙያው እንዳሉት፤ እስካሁን በተደረገ እንቅስቃሴ በ55 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የለማ ሰሊጥ ማሳ መሰብሰቡን ጠቅሰው፤እስከዚህ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ከማሳ ላይ ለማንሳት እየተሰራ መሆኑንም ተናገረዋል።

ሰሞኑን እየጣለ ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የሰሊጥ ሰብል ላይ ብክነት ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች ጊዜውን ተጠቅመው እንዲሰበስቡ እየተደረገ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከለማው መሬትም 1 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ባለሙያው አስታውቀዋል።

በመተማ ወረዳ የሽመለ ጋራ ቀበሌ አርሶ አደር አዳነ ምስጋናው እንደተናገሩት፤ በሰሊጥ ከሸፈኑት 5 ሄክታር መሬት ውስጥ 2 ሄክታሩን መሰብሰብ ችለዋል።

በዞኑ ባለፈው ዓመት በሰሊጥ ከተሸፈነው መሬት ውስጥ ግማሽ ሚሊየን ኩንታል ምርት በመሰብሰብ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደተቻለ መምሪያው ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.