Fana: At a Speed of Life!

131 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የአንድ ሰው ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ለ3 ሺህ 238 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 131 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 94 ወንዶች እና 37 ሴቶች ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ደግሞ ከ2 እስከ 80 ዓመት ውስጥ መሆኑ ተጠቁሟል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 98 ከአዲስ አበባ፣ 16 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ ከአፋር ክልል፣ ከደቡብ ክልል እና ከድሬዳዋ ከተማ ከእያንዳንዳቸው 3 ሰዎች ሲሆን ከጋምቤላ ክልል 2 እና ከትግራይ እና አማራ ክልሎች ደግሞ አንድ አንድ ሰው ነው ተብሏል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4 ሺህ 663 መድረሱን አስፍረዋል።

ሚኒስትሯ ከጠቅላላው የላቦራቶሪ ምርምራ ውስጥ 26፤ 10 ከጤና ተቋም እና 16 ከማህበረሰብ በተወሰዱ ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላቦራቶሪ ምርምራ መሆኑን በመግለፅ አንድ ናሙና ከማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል ብለዋል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥርም 75 ደርሷል ነው ያሉት፡፡

በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 84 ሰዎች ፤ 79 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ እና 1 ሰው ከደቡብ ክልል ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 297 መድሱን አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.