Fana: At a Speed of Life!

14ኛው የስልጤ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ሲምፖዚየም ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 14ኛው የስልጤ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ሲምፖዚየም በወዳጅነት አደባባይ ተከበረ፡፡
እንዲሁም የስልጤ ዞን እራሱን በራሱ ማስተዳደር የጀመረበት 20ኛ ዓመት ተከብሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ፣የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር ፣ የስልጤ ማህበረሰብን ጨምሮ የዞኑ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አንድነት ፣ ፍቅርና ህብረብሄራዊነት ማድመቂያ ናት ያሉ ሲሆን የስልጤ ብሄረሰብ ከሌሎች እህት ወንድም ህዝቦች ጋር በመሆን ከተማዋን እያለሙና እያሳደጉ ይገኛሉ ብለዋል።
በአብሮነት እና በአንድነት ከተሰራ በርካታ እድሎች እና ጸጋዎች አሉን ፤ ከተተባበርን እና ከተጋገዝን የኢትዮጵያን ብልጽግና ከማረጋገጥ ማንም የሚያስቆመን አካል እንደሌለ ምክትል ከንቲባ ገልጸዋል ።
በአዲስ አበባ ከተማም የስልጤን ማህበረሰብ የስራ ባህል እና ማንነት የሚያንፀባርቅ የባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ በከተማ አስተዳደሩ እንደሚዘጋጅ ምክትል ከንቲባዋ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ሲምፖዚየሙ በዞን ደረጃ በወራቤ ከተማ መከበሩ ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
72,089
People Reached
2,709
Engagements
Boost Post
571
58 Comments
46 Shares
Like

Comment
Share
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.