Fana: At a Speed of Life!

14ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በድሬደዋ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በድሬደዋ ከተማ ለ14ኛ ጊዜ ተካሄደ።

የሴቶች ውድድር ከማለዳው 1:30፣ የወንዶችም ደግሞ 1:45 ጀምሮ ተካሂዷል።

የሴቶችን ውድድር የድሬደዋ ምክትል ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሣራ ሃሰን፤ የወንዶቹን ውድድር ደግሞ የድሬደዋ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻኪር አህመድ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ፎዚያ ኢድሪስ አስጀምረዋል።

ውድድሩም ተጠናቋል።

በሴቶች
1ኛ ሰንበሬ ተፈሪ ከፌዴ/ማረሚያ፣
2ኛ ህይወት ገ/ኪዳን ከአልሚ ኦላንዶ፣
3ኛ ፋታው ዘራይ ከኢት/ንግድ ባንክ፣
4ኛ መሠረት ጎላ ከኢት/ኤሌክትሪክ፣
5ኛ የኔነሽ ጥላሁን ከኦሮሚያ ክልል፣
6ኛ በቀለች ጉደታ ከኦሮሚያ ክልል፣

በወንዶች
1ኛ ልዑል ገ/ስላሴ ከኦሮሚያ ፖሊስ፣
2ኛ ሲሳይ ለማ ከኦሮሚያ ፖሊስ፣
3ኛ በላይ ጥላሁን ከኢት/ንግድ ባንክ፣
4ኛ ባለው ይሁኔ ከአማራ ፖሊስ
5ኛ ኃ/ማርያም ኪሮስ ከኢት/ኤሌክትሪክ፣
6ኛ ፀጋዬ ጌታቸው ከኢት/ኤሌክትሪክ በመሆን አጠናቀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.