Fana: At a Speed of Life!

14 ሺህ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የመስኖ ፕሮጀክት እየተገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን 14 ሺህ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የአጂማ- ጫጫ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ እየተከናወነ ነው፡፡

የአጂማ-ጫጫ መስኖ ልማት ፕሮጀክት በአንጎለላ ጠራ ወረዳ በአጂማ ወንዝ ላይ ነው እየተገነባ ያለው፡፡

በ5 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የአጂማ- ጫጫ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ጋር የተያያዙ የግድብ፣ የመስኖና ድሬይኔጅ ግንባታዎች እየተከናወኑ እንደሆነም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እየተገነባ ያለው ግድብ÷ 372 ሜትር ርዝመት እና 45 ነጥብ 5 ሜትር ከፍታ እንዲሁም 55 ነጥብ 1 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በአንጎለላ፣ ጠራ እና በባሶ ወረዳ በሚገኙ 10 ቀበሌዎች ውስጥ 7 ሺህ ሔክታር በመስኖ እንደሚያለማ እና በዚህም 14 ሺህ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ነው የሚኒስቴሩ መረጃ የሚጠቁመው፡፡

በበጀት ዓመቱ የአጂማ -ጫጫ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት (ሎት-1) 20 እና (ሎት-2) 20 በመቶ፣ (ሎት-3) 34 በመቶ ለማከናወን ታቅዶ÷ በቅደም ተከተል 14 ነጥብ 24 በመቶ፣ 2 ነጥብ 14 በመቶ እና 18 ነነጥብ 81 በመቶ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

ፕሮጀክቱ በ2014 ዓ.ም ብቻ ለ4 ሺህ 639 ሰዎች የሥራ እድል መፍጠር የቻለ ሲሆን፥ ሎት-3፣ ሎት 1 እና 2 በ2016 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.