Fana: At a Speed of Life!

በሻምፒዮናው የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ ካሊ እየተካሄደ ባለው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።
በ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ የተወዳደረው አትሌት አድሃና ካሣዬ ኬኒያዊውን አትሌት ዳንኤል ኪሞዮ ተከትሎ 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን÷ 3 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ 40 ማይክሮ ሰከንድ ደግሞ ርቀቱን ለመጨረስ የወሰደበት ጊዜ ነው፡፡
በምድብ ሶስት በ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ የተወዳደረው ኤርሚያስ ግርማ 3 ደቂቃ ከ45 ሰከንድ በመግባት ከምድቡ ቀዳሚ በመሆን ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል፡፡
በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ወድድር ደግሞ ሲምቦ አለማየሁ ከምድቡ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ቀጣይ ዙር ስታልፍ መሰረት የሻነህ 2ኛ ደረጃን በመያዘ ወደ ቀጣይ ዙር አልፋለች፡፡
እንዲሁም በ800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ቅሳነት አለም 2 ደቂቃ ከ5 ሰከንድ በመግባት ከምድቡ ቀዳሚ በመሆን ወደ ቀጣይ ዙር ማለፍ ችላለች፡፡
በተመሳሳይ በምድብ አራት 800 ሜትር ማጣሪያ የተወዳደረችው ወዛም አረፋዮ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ ቀጣዩን ዙር መቀላቀሏን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.