Fana: At a Speed of Life!

15ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በአፋር፣ በደቡብ እና በድሬዳዋ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 15ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል በአፋር፣ በደቡብ እና በድሬዳዋ ተከበረ፡፡
15ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን “እኩልነትና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልፅግና!” በሚል መሪ ቃል በአፋር ክልል ደረጃ በሰመራ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሱልጣኖች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሰመራ ሎግያ እና አካባቢዋ ማህበረሰብ አካላት በተገኙበት ተከብሯል።
በበአሉ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የአፋር ክልል ርዕሰ መስዳድር ተወካይ የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሀሰን÷ የዘንድሮው በአል ላለፉት 27 አመታት የኢትዮጵያን ህዝብ በኢኮኖሚም በፓለቲካም ሲበዘብዝ የነበረው የህወሀት ጁንታን ኢትዮጵያውያን በጋራ በመተባበር ያስወገዱበት ወቅት በመሆኑ ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል።
አቶ መሀመድ በመልእክታቸው የአፋር ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ባደረገው መራር ትግል ድል በመቀዳጀት ራስን በራስ ማስተዳደር የምንችልበትን የፌደራሊዝም ስርአት እንዲሰፍን ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገ ህዝብ ነው ማለታቸውን ከአፋር ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሣሣይ ሁኔታ 15ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ቀን “እኩልነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ክልል ደረጃ የክልሉ ሕዝቦች ተወካዮች በተገኙበት በሀዋሳ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በዓሉ መከላከያ ሰራዊታችን የተቃጣበትን የክህደት ተግባር ቀልብሶ ስኬታማ የህግ የበላይነትን የማስከበር ዘመቻ ላይ መከበሩ ልዩ እንደሚያደርገው ተጠቁሟል።
በዚህ ዝግጅት ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ፣የጨፌው አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ፣አባገዳዎችና ሀደ ስቄዎች፣የሲዳማ ክልል ተወካዮችና አባቶች፣የደቡብ ክልል ብሄረሰቦች ተወካዮች፣የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣የመከላከያና ፌደራል ፖሊስ የደቡብ እዝ አመራሮች ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ ዜናም 15ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ቀን በድሬዳዋ “እኩልነትና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
በዚህ በዓል ላይ የሶማሌ ብሔራዊ ክልል እና የሐረሪ ክልል ተወካዮች የታደሙ ሲሆን÷ለክቡር ሕይወታቸው ሳይሳሱ አንጸባራቂ ድል በከሐዲው የሕወሓት ጁንታ ላይ ለተቀዳጁት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምስጋና ቀርቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.