Fana: At a Speed of Life!

15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች  በዓል በአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 15ኛው የብሄር ብሄረሰቦች  በዓል በአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ተከበረ፡፡

በዓሉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እና ሌሎች የመንግስት ስራ ሃላፊዎች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ችቦን በጋራ በመያዝ በእግር ጉዞ አክብረዋል፡፡

የእግር ጉዞው ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በቸርችል  ጎዳና እስከ  ማዘጋጃ የተካሄደ ነው።

በእግር ጉዞው ላይ ከአዲስ አበባ ምክትል  ከንቲባ እና ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በተጨማሪ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈጉባዔ  ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ  እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በበዓሉ ላይ የተለያዩ የብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ የመከላከያ ሰራዊቱ ድል ደስታ መግለጫ መርሃ ግብር መካሄዱ ነው ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም በድሉ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን ÷የመከላከያ ሰራዊት ማርች ባንድ የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎችን እያሰማ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ተዘዋውሯል።

በዚህ ወቅት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የመከላከያ ሰራዊቱ በጁንታው ላይ በተጎናጸፈው ድል እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የዘንድሮውን በዓል ልዩ የሚያደርገው በዓሉ በብሄር ብሄረሰቦች ስም ሲነግድ የነበረው ጁንታ ድል በተነሳበት ማግስት የሚከበር በመሆኑ ነው ብለዋል።

እውነተኛ ዲሞክራሲ እንዲረጋገጥ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ከንቲባዋ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ላሉ የትግራይ ተወላጆችም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

15ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የወከለውን የኢትዮጵያ የድል ብስራት ችቦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተረክቧል።

በምስክር ስናፍቅ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.