Fana: At a Speed of Life!

15 ነጥብ 1 ኪሎ ግራም የብር ጌጣጌጥ ቀረጥ ሳይከፈልበት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 22፣ 2012 (ኤፍ ቢሲ) 15 ነጥብ 1 ኪሎ ግራም  የብር ጌጣጌጥ ቀረጥ ሳይከፈልበት ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ሲሞከር ተያዘ።

ጌጣጌጡ ሊያዝ የቻለው ቀረጥ ሳይከፈልበት ከዱባይ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል በቦሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በጉምሩክ ሰራተኞች በተደረገ ፍተሻ ነው።

የብር ጌጣጌጡ ከዱባይ በተነሱ ሶስት መንገደኞች 12 ኪሎ ግራም በጃኬት መልክ በተሰራ ልብስ፣ 1 ነጥብ 1 ኪሎ ግራም በልብስ በመደብቅና፣ ቀሪው 2 ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ብር ደግሞ በድብቅ ለማስገባት ሲሞከር የተያዘ ነው።

ዋጋቸውም 16 ሺህ 724 የአሜሪካ ዶላር ሲሆን፥ በመደበኛ ታክስ ደግሞ ግምቱ  566 ሺህ 816 ብር ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የተጠረጠሩ አንድ የውጭ ሀገር  ዜጋ እና ሁለት ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.