Fana: At a Speed of Life!

15 ድርጅቶችና ባለሀብቶች ለ”ገበታ ለአገር” ፕሮጀክቶች የ255 ሚሊየን ብር የእራት ኩፖን ገዙ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፌዴራል ደረጃ ያሉ 15 ድርጅቶች እና ባለሀብቶች ለ”ገበታ ለአገር” ፕሮጀክቶች የ255 ሚሊየን ብር የእራት ኩፖን መግዛታቸው ተገለፀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በሶስት ክልሎች “ገበታ ለአገር” በሚል የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለመገንባት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግበር ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎ በምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስተባባሪነት በፌዴራል ደረጃ ያሉ 15 ድርጅቶች እና ባለሀብቶች በጠቅላላ የ255 ሚሊየን ብር የእራት ኩፖን ገዝተዋል፡፡

ይህንን ሀገራዊ እቅድ ለማሳካት የሚያግዙ የባለሀብቶች አስተባባሪ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን፥ አባላቱም አቶ አብነት ገ/መስቀል፣ አቶ ታደሰ ጥላሁን፣ ወይዘሮ ትልቅሰው ገዳሙ፣ አቶ በላይነህ ክንዴ እና አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ ተመርጠዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ድርጅቶች እና ባለሀብቶች በባለፈው ዓመት “ገበታ ለሸገር” እውን እንዲሆን ዘንድሮ ደግሞ “ገበታ ለአገር” እንዲሳካ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

በዛሬው ዕለት የእራት ኩፖን የገዙ ባለሃብቶች በበኩላቸው የሸገር ፕሮጀክት የከተማዋን ገጽታ የለወጠ እና የህዝቡን እምነት በተግባር ያረጋገጠ ፕሮጀክት በመሆኑ “ገበታ ለአገር” ፕሮጀክት እውን እንዲሆን አስፈላጊውን ተሳትፎና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.