Fana: At a Speed of Life!

16ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በድሬዳዋ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በድሬዳዋ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡
 
በዓሉ ‹‹ወንድማማችነት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
 
በአሁኑ ሰዓትም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወከሉ ብሔር ብሔረሰቦች በባህላዊ አልባሳት አሸብርቀው የተለያዩ ባህላዊ ትርዒቶችን እያሳዩ ነው፡፡
 
በአከባበር ስነ ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ህገ-መንግስታዊ እኩልነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማሳያ የሆነው ይህ በዓል በየዓመቱ ህዳር 29 ቀን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች በድምቀት ይከበራል፡፡
 
በጸጋዬ ወንደሰን
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.