Fana: At a Speed of Life!

17 ኪ.ሜ ርዝመት ያላቸው አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የኮንትራት ውል ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን 17 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው የአስፋልትና የኮብል መንገዶችን ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ዋጋ የኮንትራት ውል ተፈራርሟል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜና በጥራት ተገንብተው እንደሚጠናቀቁ የስራ ተቋራጮች የተጣለባቸውን ሀላፊነት በብቃትና በትጋት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ውል የተቀበሉት የስራ ተቋራጮች በበኩላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶቹን በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቆ ለማስረከብ ቃል የገቡ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የወሰን ማስከበር ስራዎችን በወቅቱ ከማጠናቀቅ ጀምሮ ልዩ ልዩ ድጋፎችን እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡
የኮንትራት ውል ከተፈረመላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከልም ከኮተቤ ኪዳነ ምህረት -ኮተቤ ደህንነት፣ በሻሌ ኮንዶሚኒየም አስፋልት መንገድ፣ ጥምር 8 የኮንዶሚኒየም መንገድ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፣የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የአስፋልትና የኮብል መንገዶች ግንባታ እንዲሁም ሁለት የመንገድ ዳር መብራት ፕሮጀክቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡
እነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች በአማካኝ ከ10 ሜትር እስከ 20 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያላቸው ሲሆን የመንገድ መብራት ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ከ9 እስከ 19 ወራት የሚረዝም የግንባታ ቆይታ ጊዜም እንደተያዘላቸው ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.