Fana: At a Speed of Life!

2ኛው ከተማ አቀፍ የሰላም ንቅናቄ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በየካ ክ/ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 2ኛው ከተማ አቀፍ የሰላም ንቅናቄ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ተካሄደ።

2ኛው ከተማ አቀፍ የሰላም ንቅናቄ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዛሬ በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ ተካሄዷል።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴውም “ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ፤ ለመከላከያ ሠራዊት ቅድሚያ እሰጣለሁ!” በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው።

የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን ስፖርት ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለፍቅር፣ ለጤንነት፣ ለመቻቻል፣ ለአብሮነት፣ ለልማትና ለትብብር ያለው ፋይዳ ታላቅ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለዚህም ተጠቃሚና ተሳታፊ ማህበረሰብ፣ ወጣትና ስፖርተኛ ለመፍጠር የከተማ አስተዳደሩ ከመቼውም ጊዜ በትጋት እየሰራ መሆኑን አብስረዋል።

ከማለዳው 12:00 ሰዐት ጀምሮ በከፍተኛ ንቅናቄ ከ40 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መመሪያ መሠረት በማድረግ የማስ ስፖርቱ መካሄዱን ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በቀጣይ ለሚካሄደው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ችቦ ተረክቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.