Fana: At a Speed of Life!

2 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሰባት ወራት 1 ቢሊየን 988 ሚሊየን 214 ሺህ 981 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊየን 608 ሚሊየን 582 ሺህ 897 ብር የሚገመቱ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ-ወጥ ገንዘብ ሲሆን 379 ሚሊየን 632 ሺህ 84 ብር የሚገመቱት ደግሞ የኮንትሮባንድ እቃዎችና ከሃገር ሊወጣ ሲል የተያዘ ህገ-ወጥ ገንዘብ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከሀገር ሊወጡ ሲሉ የተያዙት ኮንትሮባንድ ዕቃዎችም አደንዛኝ እፆች፣ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ፣ማዕድናት አዳዲስ አልባሳት እና ኤሌክትሮኒክስ መሆናቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙትም በ14 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መሆኑ ታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.