Fana: At a Speed of Life!

2 ነጥብ 43 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል – የኢንቨስትመንት ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት 2 ነጥብ 43 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በሰጡት መግለጫ÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3 ነጥብ 63 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ዕቅድ መያዙን ጠቁመው÷ 2 ነጥብ 43 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ18 ነጥብ 3 በመቶ እድገት ማሳየቱንም ነው ኮሚሽነሯ በመግለጫቸው ያነሱት፡፡

203 ባለሀብቶች ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገቡ ታቅዶ 118 ባለሀብቶች መሰማራታቸውን ገልጸው፥ ከዚህም ውስጥ 65ቱ በማኑፋክቸሪንግ 50 ያህሉ ደግሞ በአገልግሎትና ሦስቱ በግብርና ዘርፍ መሰማራታቸውን አብራርተዋል፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ከሚላኩ ምርቶች 223 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት መታቀዱን እና 156 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ27 ሚሊየን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በመግለጫቸው አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.