Fana: At a Speed of Life!

12 ሺህ ዶላር እና ከ58 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ጉምሩክ እና በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች 12 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እና ከ58 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ተገለጸ፡፡

የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ከታኅሳስ 21 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ከጅግጅጋ ወደ ቶጎ ውጫሌ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ  ላይ በተደረገ ፍተሻ 12 ሺህ  ዶላር እና ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ከ32 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በሕገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ በተለያዩ ኬላዎች መያዛቸውን ከጉምሩክ ኮሚሽን  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ድርጊቱን ለመግታት በሚደረገው  እንቅስቃሴ  ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም  የጉምሩክ ኮሚሽን መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/

ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.