Fana: At a Speed of Life!

21ኛው ታላቁ ሩጫ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገውና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው 21ኛው የሩጫ ውድድር በሰላም ተጠናቋል፡፡
ዛሬ የተካሄደው የታለቁ ሩጫ ውድድር በሠላም መጠናቀቁ ኢትዮጰያ ሰላም አይደለችም የሚል መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን መረጃቸው ትክክለኛ ያልሆነና ሀሰተኛ መሆኑን ያረጋገጠ ከመሆኑም ባሻገር ከተማችን አዲስ አበባ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባትና መሰል ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ምቹ መሆኗን የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡
በመጪው ሳምንት ኢትዮጵያ 35ኛውን የአፍሪካ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ የምታስተናግድ ስለሆነ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።
የመዲናዋ ፖሊስ የዛሬው ውድድር በሠላም እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ አካላትና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት ምስጋና ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.