Fana: At a Speed of Life!

በአምስት ቀናት ውስጥ ከ43 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአምስት ቀናት ውስጥ ከ43 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ።

ከግንቦት 1 እስከ 5 የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ፣ ዶላር ፣ የህብረተሰቡን ሠላም የሚያናጉ ጥይቶችና መሳሪያዎች ከእነድርጊት ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ሚኒስትሩ ለፌዴራል ፖሊስ ፣ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ ለሁሉም ክልሎች የፀጥታ አካላት እና የክልል አመራሮች እንዲሁም አስፈላጊውን ትብብር ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.