Fana: At a Speed of Life!

215 ዜጎች ከቤሩት ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 215 ኢትዮጵያውያን ከቤሩት ወደ ሃገራቸው ተመለሱ፡፡

በቤሩት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውና በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን ያለቅጣት ወደ ሃገራቸው ይመለሱ ዘንድ በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤትከሃገሪቱ መንግስት ጋር መግባባት ላይ መድረሱ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት በታህሳስ ወር ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ተመዝግበው ከነበሩ 1 ሺህ 239 ዜጎች መካከል 215 ዜጎች ከሊባኖስ ከተማ ወደ ሃገራቸው መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተያያዘም 339 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.