Fana: At a Speed of Life!

238 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በአሸባሪው ህወሓት ዘረፋና ውድመት ተፈጽሞባቸዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በወረራ ይዟቸው በነበሩ አካባቢዎች በ238 የባንኩ ቅርንጫፎች ላይ ዘረፋና ውድመት መፈፀሙን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።
 
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ እንደገለጹት÷ የሽብር ቡድኑ በወረራ በገባባቸው አካባቢዎች በባንኩ ሰራተኞች ላይ ግድያ እንዲሁም በተቋሙ ላይ ዘረፋና ውድመት ፈፅሟል።
 
ከአሸባሪው ወረራ ነጻ በወጡ አካባቢዎች የባንኩ ቅርንጫፎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው አረጋግጠናል ያሉት የባንኩ ፕሬዚዳንት÷ በመቀሌ የሚገኙት 61 እና በሽሬ 59 የባንኩ ቅርንጫፎች ያሉበት ሁኔታ እስካሁን አይታወቅም ብለዋል።
 
የሽብር ቡድኑ ገንዘብ፣ ኮምፒውተር፣ ጀኔሬተሮችና ሌሎች ንብረቶችን በመዝረፍ የኤ ቲ ኤም ማሽኖችን በመስበርና በማውደም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አብራርተዋል።
 
ከወራሪው ነፃ በወጡ አካባቢዎች በባንኩ ቅርንጫፎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በዝርዝር ለማወቅና ዳግም ስራ ለማስጀመር የጥናት ቡድን መሰማራቱን ገልጸዋል።
 
በባንኩ ቅርንጫፎች ላይ የሰነድና የንብረት ውድመት ቢደርስም የደንበኞች መረጃ ግን ሙሉ በሙሉ ማዕከል ላይ ስለሚገኝ ደንበኞች “መረጃዬ ይጠፋል” የሚል ምንም አይነት ስጋት ሊኖራቸው አይገባም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ከአሸባሪው ህወሓት ነፃ በወጡ አካባቢዎች እስካሁን 12 የባንኩ ቅርንጫፎች ዳግም ስራ መጀመራቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ÷ በቅርቡ ደግሞ 30 የሚሆኑትን ስራ ለማስጀመር ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.