Fana: At a Speed of Life!

24 የተጓተቱ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ቢሮ በክልሉ በተለያዩ  አካበቢዎች ግንባታቸው የተጓተቱና የመልካም አስተዳደር ችግር ፈጥረው የነበሩ 24 የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ማጠናቀቁን ገለጸ።

በቢሮዉ የመጠጥ ውሃ ግንባታ ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሎላሞ ሱላሞ እንደገለጹት ÷የንጹህ መጠጥ ዉሃ እጥረት ያሉባቸዉን የክልሉን አካባቢዎች በመለየትና ትኩረት በመስጠት ማድረግ ሁሉንም ዜጋ  ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ነው።

የውሃ አስፈላጊነት ለመሠረታዊው የመጠጥ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ለኢኮኖሚ ብልጽግና ለማረጋገጥም ወሳኝ ሚና ያለው በመሆኑ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቁ የውሃ ተቋማትን ህብረተሰቡ ሊንከባከባቸው እንደሚገባም መግለፃቸውን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.