Fana: At a Speed of Life!

125ኛው የዓድዋ ድል በዓል ማጠቃለያ ”የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ አድዋ እንደ ማሳያ” በሚል መሪ ቃል ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛው የዓድዋ ድል በዓል ”ዓድዋ የኅብረ ብሔራዊ አንድነት አርማ” በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 1 አስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ እና የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለበት ሀገር ሁሉ በልዩ ልዩ ዝግጅት ሲከበር ቆይቷል።
የድል በዓሉ የማጠቃለያ መርኃ ግብርም ከዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ጋር በማስተሳሰር ”የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ አድዋ እንደ ማሳያ” በሚል መሪ ቃል በስዕል ዐውደ ርዕይ፣ በስነ ፅሁፍ፣ በጥናታዊ ፅሁፍ እና በቲያትር ተከብሯል።
ጉባኤውን የከፈቱት ዶክተር ሂሩት ካሳው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ”ዓድዋ የጀግና እናቶቻችን ተጋድሎ ውጤት ነው” ብለዋል።
እናቶቻችን በዓድዋ ጦርነት ወቅት የጦር መሃንዲስ ሆኖ በማማከር፣ ጦር መዞ ጎራዴ ስቦ በመዋጋት፤ አርበኞችን በማነቃቃትና በማስደሰት፣ ስንቅና ትጥቅ በማዘጋጀት እና ቁስለኞችን በማስታመም ትልቁን ተጋድሎ ፈፅመው ኢትዮጵያ ሀገራችንን የሀገር አውራ እንድትሆን አድርገዋል።
እንደ እቴጌ ጣይቱ ዓይነት ጀግኖች እናቶቻችን በጦርነቱ በሁለንተናዊ ተሳትፎ ባይሳተፉ ኖሮ ዓድዋን ማሰብ አይቻልም ነበርም ነው ያሉት።
በማለት በአድዋ ጦርነት ወቅት እና እስካሁን ባለው የሀገር ግንባታ የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ግንባር ቀደም እንደሆነ ተናግረዋል።
በእንግድነት የተገኙት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ዩሚኮ ዮኮዞኪ ÷ ስለአድዋ ድል በዓል በምናስብበት ጊዜ ከንጉሱ ጋር ሁሌ የምትታይ አንዲት ሴት እናያለን ብለዋል።
ይህች ሴት ማናት? ብለን ስንጠይቅ የአድዋ ድል የጦር መሀንዲስ፣ ጥበበኛ እና አርበኛ እቴጌ ጣይቱ መሆኗን አወቅን ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በሁሉም ዘርፍ የሴቶች ሚና ከጎላ መጨረሻው ሰላምና ድል ይሆናልም ነው ያሉት።
አያይዘውም ”እናንተ ዕድለኞች እንኳን ለ125ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ አድዋን እና ሴቶችን በተመለከተ አራት ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎች አስተያየት እና ሀሳብ ቀርቦ በዶክተር ሂሩት ካሳው ማጠቃለያ ተሰጥቶበት መርሀ ግብሩ መጠናቀቁን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.