Fana: At a Speed of Life!

286 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 286 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
መንግስት በችግር ላይ ያሉ ዜጎችን ከተለያዩ የዓረብ ሀገራት በተለይም ከሳዑዲ ዓረቢያ የማስመለሱን ስራ አጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።
በዚህም ትናንት 286 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ተደርጓል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለተመላሾች አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.