Fana: At a Speed of Life!

3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ነገ በአማራ ክልል ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል የ2013 ዓ.ም የ3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ነገ ይካሄዳል።
ክልሉ በ3ኛው ዙር መርሃ ግብር 1 ነጥብ 83 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል አቅዷል።
በክልሉ ሃምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 247 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ማቀዱ ታውቋል፡፡
የክልሉ የግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ማርቆስ ወንዴ የሚተከሉ ችግኞች የት እንደሚተከሉ የመከታተያ ስርዓት ተዘርግቷል ብለዋል፡፡
ለአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 35 ሺህ ሄክታር መሬት ተለይቷል ነው የተባለው።
ሃላፊው የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለየት የሚያደርገው ኢትዮጵያ በ2ኛው ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በምታካሂድበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ለአጎራባች ሃገራት ችግኝ የማቅረብ ስራ የሚሰራ በመሆኑ የተለየ ያደርገዋል ነው ያሉት አቶ ማርቆስ ።
በነገው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር የሚተከሉ ችግኞች የሃገር በቀል ችግኞችና ፍራፍሬዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በምስክር ስናፍቅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.