Fana: At a Speed of Life!

3ኛው የአፍሪካ ሴቶች ጉባኤ በኒጀር ኒያሚ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በአፍሪካዉያን ሴቶች ላይ ብቻ የሚያተኩረው 3ኛው የአፍሪካ ሴቶች ጉባኤ በኒጀር ኒያሚ መካሄድ ጀምሯል።
በዚሁ ስብሰባ የአፍሪካውያን ሴቶች በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፏቸዉ እንዲረጋገጥ ለማድረግ እንዲሁም የሴቶች መብት ረገጣ እና እየጨመረ የመጣውን ያለ እድሜ ጋብቻ ለመከላከል ያለመ ምክክር እየተደረገ ነው።
የስብሰባው ተሳታፊ ሴቶችም ለአፍሪካ መሪዎች እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያለእድሜ ጋብቻን በመከልከል መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ኒጀር ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር እድገት በማስመዝገብ ቀዳሚዋ ሃገር ስትሆን አንዲት ሴት በአማካይ 7 ነጥብ 5 ልጆች ይኖራታል ነው የተባለው፡፡
ይህም ወጣት ልጃገረዶች ያለ እደሜያቸው እንዲያገቡ እና ትምህርት እንዲያቋርጡ ምክንያት መሆኑን ዘ ኢስት አፍሪካ ኒውስ በዘገባዉ አስታወቋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.