Fana: At a Speed of Life!

3 ሺህ 375 የክላሽንኮቭ ጥይቶችን እና 783 የብሬን ጥይቶችን ደብቆ ሊያሳልፍ የሞከረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ክትትል ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ።
በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 የሚኖር እሸቴ ፀጋዉ የተባለ ተጠርጣሪ ከጎንደር ከተማ ወደ ባህር ዳር ከተማ በኮድ 2 አማ 24492 ዳማስ መኪና ሻግ በማሰራት በርካታ ጥይቶችን ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ማዕከላዊ ጎንደር ኢንፍራንዝ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡
ተጠርጣሪዉ 3 ሺህ 375 የክላሽንኮቭ ጥይቶችን እና 783 የብሬን ጥይቶችን ደብቆ ሊያሳልፍ ሲሞክር እጅ ከፍንጅ መያዙን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ዉስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻም ተጨማሪ አንድ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ2 ሺህ 100 ጥይቶቻ ጋር ተይዟል ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.