Fana: At a Speed of Life!

ሦሥት የፊዚክስ ሊቃውንት የ2021 የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በስዊድን ስቶኮልም በሚገኘው “የስዊድን ሮያል ሳይንስ አካዳሚ” በተሰየመው የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ በፊዚክስ ዘርፍ አሸናፊ የሆኑ ሶስት ሊቃውንቶች ተሸላሚ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

ትውልደ ጃፓናዊ የሆነው አሜሪካዊ ሳዩኩሮ ማናቤ፣ ጀርመናዊው ክላውስ ሃስልማን እና ጣሊያናዊው ጂዮርጂዮ ፓሪሲ የ2021 የፊዚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

ሽልማቱን ያሸነፉትም በምድር ላይ እየተከሰተ ያለውን ውስብስብ መልክዓ ምድር እና የዓየር ንብረት ለውጥ በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ጉልህ አስተዋፅዖ በማበርከታቸው ነው ተብሏል፡፡

ከሽልማቱ ግማሽ ያህሉ ማለትም 1ነጥብ 15 ሚሊየን ዶላር በዜግነቱ አሜሪካዊ ለሆነው የ90 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ሳዩኩሮ ማናቤ እና በምድር የዓየር ንብረት ለውጥ እና በዓለም ሙቀት መጨመር ላይ ለሠራው ጀርመናዊ ሃስልማን እኩል እንደሚከፋፈል ተመላክቷል፡፡

ቀሪው ግማሽ የሽልማቱ ገንዘብ ደግሞ ለጣሊያናዊው የፊዚክስ ሊቅ ጂዮርጂዮ ፓሪሲ እንደሚሸለም ተገልጿል፡፡

ጣሊያናዊውን የፊዚክስ ሊቅ ለአሸናፊነት ያበቃው ግብታዊ የአየር እና ፈሳሽ እንቅስቃሴ እና እሽክርክሪት ድብቅ መስለው የቆዩ ህጎችን በጥናት በማግኘቱ ነው ሲል ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል፡፡

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.