Fana: At a Speed of Life!

34 የባቡር ካፒቴኖች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር 34 የባቡር ካፒቴኖችን አስመርቋል።

ካፒቴኖቹ ለሁለት ዓመታት ሥልጠና ያገኙ ሲሆን ለ6 ወራት ወደ ቻይና አቅንተው የተግባር ልምምድ ማድረጋቸው ተገልጿል።

CCEC እና CERC የተሰኙት የቻይና ኩባንያዎች በጥምረ ከአክሲዮን ማኅበሩ ጋር በገቡት ውል መሠረት የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ሽግግር ለመፍጠር የሚያግዝ ሥልጠና በመስጠት ተማሪዎችን ለምረቃ አብቅተዋል ተብሏል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፥ በኢትዮጵያ የባቡር ዘርፉ ዕድገት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸው በ2011 ዓ.ም 821 ሺህ ቶን የነበረው የማንሣት አቅም በ2012 ወደ 1 ነጥብ 03 ሚሊየን ቶን ዕድገት አሳይቷል ብለዋል።

በዘንድሮው በጀት ዓመት በ9 ወራት አፈጻጸሙ ወደ 1 ነጥብ 23 ሚሊየን ቶን ከፍ ማለቱን ሚኒስትሯ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የዘርፉ ዕድገት በሀገሪቱ አጠቃላይ ወጪ ገቢ ንግድ ላይ የሚኖረው ሚና እንዲጎላም ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸጸዋል።

ተመራቂዎችም ከሥልጠና ያገኙትን ዕውቀት እና ክህሎት ተጠቅመው ሀገሪቱን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ጥላሁን ሳርካ በበኩላቸው በአክሲዮን ማኅበሩ እና በቻይና ሁለት ድርጅቶች ጥምረት የሚሰጠው ስልጠና ቀጣይነት እንደሚኖረው አንስተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.