Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጅማና ዳውሮ ጉብኝት አድርገዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በጅማ  እና ዳውሮ ጉብኝት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጅማ አባ ጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በአባ ገዳዎች፣ በሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በአቀባበሉ ላይም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ለሌሎችም እንግዶች የተለያዩ ስጦታዎች እንደተበረከቱም ከጅማ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከውጭ ሀገራት ባለሀብቶች ጋር በመሆን በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞንም ጉብኝት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከውጭ ሀገራት ባለሀብቶች ጋር በመሆን በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞንም ጉብኝት አድርገዋል።
በጉብኝታቸውም የዳውሮ ተፈጥሯዊ ሀብቶችንና በኮይሻ ወረዳ እየተገነባ ያለውን የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ተመልክተዋል።
በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ከሚለሙት አካባቢዎች መካከል አንዱ የሆነው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በልዑካቸው የተጎበኘ ሲሆን ከኮይሻ እስከ ንጉስ ሀላላ ኬላ ያሉ የተፈጥሮ መስህቦችም ተጎብኝተዋል።
የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም 36 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን ሲጠናቀቅ 2160 ሜጋዋት የማመንጨት አቅም ይኖረዋል።
በተያያዘም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ ግድብንም ጎብኝተዋል።
ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት እስከ 60 በመቶ እየሸፈነ የሚገኝ ትልቁ ኃይል ማመንጫ ነው።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.