Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ዊቻትናቲክቶክ ላይ ከእሁድ የሚጀምር እገዳ ጣለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ ዊቻት እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዕውቅናው እየናኘ የመጣው ቲክቶክ ዳውንሎድ እንዳይደረጉ ከእሑድ የሚጀምር እገዳ መጣሏን አስታወቀች፡፡

ይህ የተሰማው የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ ተከትሎ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

የንግድ አስተዳዳሪው ክፍል እንደገለጸው ከሆነ ዊቻትና ቲክቶክ የመተግበሪያ ግብይት ማዕከል ውስጥ ወይንም አፕ ስቶር ላይ ማስቀመጥ የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ከፊታችን እሑድ ጀምሮ ለዊቻት እንዲሁም ከህዳር መጀመሪያ ጀምሮ ለቲክቶክ ኢንተርኔት ማቅረብ እና ማስተላለፍ እንደማይፈቀድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የንግድ ሚኒስትሩ ውሳኔውን ተከትለው እንደተናገሩት ትራምፕ የአሜሪካንን ብሔራዊ የፀጥታ ጉዳይ አስመልክተው ያሳለፉት ውሳኔ አካል መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም ሌሎች ፕሮግራማቸው ላይ እክል ያለባቸው ኩባንያዎች እገዳ እንደሚጣልባቸው የንግድ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.