Fana: At a Speed of Life!

1  ሺህ 72 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ዛሬ በተደረገው ሶስት በረራ 1  ሺህ 72  ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በመጀመሪያው በረራ 348 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ፥ በሁለተኛው በረራ 354 ዜጎች  እንዲሁም በሶስተኛው በረራ 370 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በመጀመሪያ እና በሁለተኛ በረራ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ዜጎች  ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ÷በሶስተኛ በረራ ከተመለሱ 370 ዜጎች መካከል ደግሞ 247ቱ ሴቶች ፣94ቱ ህጻናት እና 29 ወንዶች  መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መንግሥት በሳዑዲ አረቢያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና 16 መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን በአባልነት ያቀፈ ብሔራዊ  ኮሚቴ  በማዋቀር  102 ሺህ ዜጎችን ወደ ሃገር ለመመለስ በማቀድ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.