Fana: At a Speed of Life!

36ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 37ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ነገ በጃንሜዳ ይካሄዳል።

በውድድሩ አምስት ክልሎች፣ ሁለት የከተማ አስተዳደሮች፣ 37 ክለቦች እና የማሰልጠኛ ተቋማት የሚሳተፉ ይሆናል።

6 ኪሎ ሜትር ወጣት ሴቶች ፤ በ10 ኪሎ ሜትር አዋቂ ሴቶች፣ በወንዶች 8 ኪሎ ሜትር ወጣት ወንዶች፣ በ10 ኪሎ ሜትር አዋቂ ወንዶች ፣በድብልቅ ሪሌ በ8 ኪሎ ሜትር ሴቶች እና ወንዶች ውድድሩ የሚካሄድባቸው ሁነቶች ናቸው።

የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች አጠቃላይ ሽልማት 400 ሺህ ብር ማዘጋጀቱ ተገልጿል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.