Fana: At a Speed of Life!

ለአንድ ዓመት የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት ሲፈጽም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአንድ ዓመት የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት ሲፈጽም የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ።

የሀይል ስርቆቱን ሲፈፀም የቆየው ግለሰብ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ዮቴክ ኮንስትራክሽን ህንጻ አካባቢ መሆኑ ተገልጿል ።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ ÷ ተጠርጣሪው ግለሰብ በእንጀራ ንግድ ላይ የተሰማራ መሆኑን ገልጸዋል።

ግለሰቡ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንብ እና አሰራር ውጪ የኤሌክትሪክ ሃይል ከቀጥታ መስመር በመቀጠል ለ365 ቀናት ያለአግባብ ሲጠቀም መቆየቱንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቁጥጥር ሰራተኞ ወደቦታው ሄደው ባደረጉት ማጣራት ግለሰቡ በገንዘብ ሲተመን 55 ሺህ 668 ብር በድርጅቱ ላይ ጉዳት ማድረሱን እና ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.